በትምህርት ሻምፒዮን ኔትዎርካችን አማካኝነት፣ በማህበረሰባቸው ያሉትን ሴት ልጆች ችግር በሚገባ የሚረዱአስትማሪዎች እና ተሟጓቾች ላይ ኢንቬስት እናደርጋለን፡፡ በእነዚህም ክልልሎች የሚገኙት ሴቶች የሁለተኛ ደረጃትምህርት ማግኘት ያልቻሉ ናቸው፡፡
በአካባቢያዊ፣ በብሄራዊ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ሴት ልጆች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማግኘት እንዲችሉ፣ የትምህርትማበረታቻ ቁሳቁሶች እንዲሟሉላቸው እና ፓሊሲ ለውጦችን ለማምጣት እንሟገታለን፡፡የምናገለግላቸው ሴት ልጆችለህይወታቸው ትልቅ አላማ ያላቸው ሲሆን እኛም እነሱን
ከሚያግዟቸው መሪዎች ትልቅ ነገርን እንጠብቃለን፡፡
ሴቶች እራሳቸውን ወክለው ምን መማር እንደሚፈልጉ አና አቅማቸውን ለማውጣት ምን እንደሚያስፈልጋቸውለመሪዎች በቀጥታ መናገር እንዳለባቸው እናምናለን፡፡ እኛም የሴት ልጆችን ድምጽ ለማጉላት ከውሳኔ ሰጪዎች ጋርበስብሰባ፣ በዲጂታል ህትመቶቻችን እና በመጽሄታችን ተጠቅመን በቀጥታ
በማገናኘት፣ ታሪካቸውን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን፡፡
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴት ልጆች ተማሩ ማለት ብዙ ስራ ለመስራት የሚች ሴቶች ተፈጠሩ ማለት ነው፤፡ ይህም ለአለምአድገት 12 ትሪሊዮን ዶላር ያህል ተጨማሪ ገቢ የማመንጨት አቅም አለው፡፡
የተማሩ ሴቶች ያለእድሜ ጋብቻ የማድረግ እና በ ኤችአይቪ ኤድስ የመያዝ አዝማሚያቸው እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ ጤናማእና የተማሩ ልጆችን የማሳደግ አቅማቸው ደግሞ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ እያንዳንዷ ሴት ልጅ አንድ ተጨማሪ ክፍልባጠናቀቀች ቁጥር የህጻናት ሞት እና ያለእድሜ ጋብቻ መጠንም በዛው ልክ እየቀነሰ ይመጣል፡፡
አንድ ሃገር ለሁሉም ልጆቹ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን መስጠት ከቻለ፣ ወደ ጦርነት የመግባት እድሉን በግማሽይቀንሳል፡፡ በአለም ዙሪያ ደህንነትን ለማስጠበቅ ትምህርት ዋነኛው መሳሪያ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አክራሪነት/ጽንፈኝነት ብዙ ጊዜ የሚሰፍነው እኩልነት በማይጠብቀበት ቦታ ላይ ስለሆነ ነው፡፡
የብሩኪንግስ ኢንስቲትዩሽን ለሴቶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መስጠት ገንዘብ ቆጣቢ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያመሳሪያ ነው ይለዋል፡፡ ተጨማሪ ጥናቶችም እንዲሁ የሴቶች ትምህርት አንድ ሃገር ለተፈጥሯዊ አደጋ ያለውንተጋላጭነት በሰፊው ይቀንሰዋል ይላሉ፡፡
መላላ ፈንድ ሴቶች ከትምህርት የመስተጓጎል እድላቸው በጣም ከፍተኛ በሆነባቸው ሃገራት ላይ ለሴት ልጆች ትምህርትየሚሟገቱ ሰዎች እና አስተማሪዎች ላይ ኢንቨስት ያደርጋል፡፡
ሴት መምህራንን መመልመል እና ስነ-ጾታዊ መድሎን ማስወገድ
ምርምሮችን በማካሄድ እና ለመምህራን እና ለወጣት መሪዎች ስልጠና በመስጠት፣ ኢንዲጂነስ/ሃገር በቀል እና አፍሮብራዚላዊ ሴቶች ትምህርት የሚያገኙባቸውን እድሎች ማመቻቸት
ሴቶች ወደፊት እንዳይራመዱ አስረው የሚይዟቸውን መሰናክሎች ለመስበር፣ መንግስት ያለእድሜ ጋብቻን እንዲያግትማስተባበር፣ ደህንነታቸው የተጠበቁ ትምህርት ቤቶች እንዲኖሩ መመሪያዎችን ማቋቋም እና የትምህርት ቤትተደራሽነትን ለማሻሻል የትምህርት ተሟጋቾች ኔትዎርክ መዘርጋት
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በነጻ የማግኘት እድልን ለማስፋፋት መሟገት ፣የሜንቶርሺፕ ፕሮግራሞችን መተግበር እና ሴቶችን በድጋሚ ትምህርት የማስመዝገብ ዘመቻዎችን ማካሄድ
ያለእድሜ ጋብቻን ለመቀነስ መሟገት እና ከትምህርት ገበታቸው የተስተጓጎሉ ሴት ልጆች ትምህርታቸውን እንዲቀጠሉበደጋፊ ፕሮግራሞች እና በዲጂታል ትምህርቶች ማገዝ
በቦኮሃራም ስጋት ስር የሚኖሩ ሴት ልጆች ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ማገዝ እና ለ12 አመታት ነጻ፣ ደህንነቱ እና ጥራቱየተጠበቀ ትምህርት ለሁሉም ሴቶች እንዲዳረስ ዘመቻ ማድረግ
የትምህርት ፈንድ ለማግኘት መጣር፣ ለሴት ልጆች ትምህርት ቤቶችን መገንባት እና ወጣት ሴቶች መብታቸውንለማስከበር እንዴት መታገል እንዳለባቸው ማሰልጠን
የሲሪያ ስደተኛ ሴት ልጆች ቴክኖሎጂ እና የማህበራዊ አውትሪቾችን በመጠቀም እንዴት ለትምህርት መመዝገብእንደሚችሉ ማሳየት እና አስተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደቱን ለስደተኞች እንዴት ማመቻቸት እንዳለባቸውማሰልጠን
መላላ ዩሳፍዚ የመላላ ፈንድ ተባባሪ መስራች እና የቦርድ አባል ስትሆን፣ የትምህርት ዘመቻዋን የጀመረችው የ11 ዓመት ታዳጊ ልጅ ሆና ነበር፡፡ በስም አልባ ብሎጓ በመጠቀም በፓኪስታን ስዋት ሸለቆ ውስጥ በታሊባን አመራር ስር ስላለው አስከፊ ህይወትም ለቢቢሲ በሚስጥር ዘግባለች፡ በአባቷ የአክቲቪዝም ስራ የተደመመችው መላላ ብዙም ሳትቆይ ለሴቶች ትምህርት በይፋ መሟገት ጀመረች፤ ብዙ የአለም አቀፍ ሚዲያን ቀልብም መሳብ ቻለች፣ ብዙ ሽልማቶችንም አገኘች ፡፡
በይፋ ነገሮችን ደፍራ በመናገሯ ምክንያት በ15 አመቷ በታሊባን አጥቂዎች በጥይት ተመታች፡፡ በዩናይትድ ኪንግደም ከጥቃቱ ካገገመች በኋላ ለሴቶች ትምህርት መታገሏን ቀጠለች፡፡ በ2013ዓ.ም ከአባቷ ዚአውዲን ጋር አንድ ላይ በመሆን መላላ ፈንድንም መሰረተች፡፡ ከአንድ አመት በኋላ የኖብል ፕራይዝን በመሸለም ሁሉም ሴት ልጆች የ12 ዓመት ደህንነቱ እና ጥራቱ የተጠበቀ ነጻ ትምህርት እንዲያገኙ ለምታደርገው ጥረት እውቅና አገኘች፤፡ መላላ ከኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ በፊሎዞፊ፣ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚክስም በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃለች፡፡
ዚአውዲን ዩሳፍዚ የመላላ ፈንድ ተባባሪ መስራች፣ የቦርድ አባል እና የመላላ አባት ነው፡፡ ለብዙ አመታት በገዛ ሃገሩ ፓኪስታን መምህር እና የትምህርት ቤት አስተዳዳሪ በመሆን አገልግሏል፡፡ ታሊባኖች በስዋት ሸለቆ የሚገኘውን መኖሪያቸውን ሲወሩ፣ ቆራጡ ዚአውዲን በሰላማዊ መንገድ የሰዎችን የግል መብት ለመገደብ የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች ይቃወም ነበር፡፡ በይፋ ነገሮችን ሳይፈራ መናገሩ ዚአውዲንን አደጋ ውስጥ ቢጥለውም፣ ዝም ማለት ግን የባሰው አደጋ እንደሆነ ያምን ነበር፡፡ በአባቷ ምሳሌ የተነሳሳችውም መላላ፣ በይፋ ሴት ልጆች ትምህርት ቤት መሄድ እንዲችሉ የራሷን ዘመቻ ጀመረች፡፡
እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በኦክቶበር 2009 ዓ.ም የኒውዮርክ ታይምስ ስለዚአውዲን እና መላላ በስዋት ለሴቶች ትምህርት መሳካት ስለምታደርገው ትግል የሚያሳይ አጭር ዶክዩመንታሪ ቀረጸ፡፡ እያደገ በመጣው ታዋቂነቷ/ተደማጭነቷ የተነሳ፣ ከ2 ዓመት በኋላ መላላ በታሊባን አጥቂዎች አናቷ ላይ በጥይት ተመታች፤ ከሞት አፋፍ ተርፋም ለህክምና ወደዩናይትድ ኪንግደም ተወሰደች፡፡ ትግሉን በወኔ ለመቀጠል የወሰኑት ዚአውዲን፣ ባለቤቱ ቱር ፔካይ እና ሁለት ወንድ ልጆቻቸው መላላን በርሚንግሃም ላይ ተቀላቀሏት፡፡ በ2013 ዓ.ም፣ ዚአውዲን እና መላላ አንድ ላይ በመሆን መላላ ፈንድን መሰረቱ፡፡ ሁለቱም በህብረት እያንዳንዷ ሴት ልጅ የ 12 አመት ደህንነቱ እና ጥራቱ የተጠበቀ ነጻ ትምህርት የማግኘት መብቷን አጥብቀው ይደግፋሉ፡፡